“ንባብ ለሕይወት” ግዙፉ አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ ግዙፉ የመጽሐፍ አውደ ርዕይ “ንባብ ለሕይወት ” የመጽሐፍና ንባብ አውደ ርዕይ ከቀናት በኃላ ሊካሄድ እንደሆነ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

“ንባብ ለሕይወት” የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዘንድሮ ከሐምሌ 24 እስከ ሐምሌ 27 2017 ዓ.ም ድረስ ለቀናት መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ውስጥ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል።

የንባብ ከሕይወት ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በመተባባር ባዘጋጀው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በርካታ ደራሲያን በመገኘት መጻሕፋቸውን ያስተዋውቃሉ ተብሏል።

የመጻሕፍት አሳታሚዎችና አከፋፋዮች መጻሕፍትን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ።

በአውደ ርዕዩ ላይ የመጽሐፍ ምርቃትና ሀሳብ ማንሸራሸሪያ ልዩ ልዩ መድረኮች ተዘጋጅቷል።

የአውደ ርዕዩ መግቢያ በነፃ ሲሆን ሐሙስ ሐምሌ 24 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ይከፈታል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...