ንግድ ባንክ በሲቢኢ ኑር  የሰበሰበው ገንዘብ ከ200 ቢሊዮን ብር አለፈ

Date:

በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ በመሆን ከ11 ዓመታት በፊት የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአሁኑ ጊዜ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ አስቀማጭ ደንበኞችን በማፍራት የተቀማጭ ገንዘቡን ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል። 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተቀማጭ ገንዘብ ከኢንዱስትሪው የ51.3 በመቶ ድርሻ መያዝ ችሏል።

ባንካችን በሲቢሲ ኑር ከወለደ ነፃ የባንክ አገልግሎት ባለፉት 11 ዓመታት ከ150 ቢሊዮን ብር በላይ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለተሠማሩ ደንበኞች የፋይናስ አቅርቦት ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በዚሁ ዘርፍ ተሰጥቶ የሚገኘው ጠቅላላ የብድር መጠን ከ79.2 ቢሊዮን ብር በላይ ነው።

ባንካችን ከወለድ ነፃ ፋይናንሲንግ ዘርፉም የኢንዱስትሪውን 48 በመቶ ድርሻ በመያዝ በመምራት ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዚህ ስኬት ላበቁን ደንበኞች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምስጋናውን ያቀርባል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...