ይህም ከቀዳሚው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ85 በመቶ ብልጫ አለሁ ብሏል፡፡
አማራ ባንክ ይህንን ያለው የባለአክስዮኖች 4ተኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው።
ጠቅላላ የባንኩ ሀብት 43.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን የተናገሩት የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ዩሀንስ አያሌው ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ23.2 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል ብለዋል።
በተጨማሪም ባንኩ የሰጠው ብድር በ29 በመቶ አድጎ 25.5 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተጠቅሷል፡፡
የአማራ ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን በ26 በመቶ አድጎ 31.5 ቢሊዮን ብር ድርሷል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የባንኩ አጠቃላይ ገቢም በ29 በመቶ አድጎ 5.6 ቢሊዮን ብር ድርሷል ተብሏል፡፡
አማራ ባንክ በአሁኑ ሰዓት 1 ሚሊየን የሚጠጉ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች እንዳሉት የተናገረ ሲሆን በአጠቃላይ የአገልግሎቴ ተጠቃሚዎች ወደ 2.4 ሚሊየን ደርሷል ብሏል።
በተጨማሪም በተያዘው በጀት አመት 3.6 ቢሊየን ያልተጣራ ትርፍ ለማግኘት በእቅድ መያዙን የተናገሩት የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ዩሀንስ አያሌው የውጭ ምንዛሬ ሀብት ግኝት በተመለከተ ደግሞ 250 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ ላይ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።
