አሜሪካ ለዲቪ ምዝገባ 1 ዶላር ልትጠይቅ ነው

Date:

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ሎተሪ ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ዶላር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

ይህ የማይመለስ ክፍያ ከDV-2027 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ መሥሪያ ቤቱ ይህን ለውጥ ያመጣው የሎተሪውን የማስተዳደር ወጪ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመከፋፈል ታስቦ እንደሆነ አስረድቷል።

ቀደም ሲል የ330 ዶላር የኢሚግሬሽን ቪዛ ክፍያ የሚከፍሉት የተመረጡት ብቻ ሲሆኑ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያልተሳኩ አመልካቾች ምንም ሳይከፍሉ ይቆዩ ነበር።

አሁን ባለው አሰራር ግን በግምት 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ዓመታዊ ተመዝጋቢዎች እያንዳንዳቸው 1 ዶላር በመክፈል፣ ወጪው በ55,000 አሸናፊዎች ላይ ብቻ ከመውደቅ ይልቅ በእኩል እንዲሰራጭ ያግዛል ተብሏል።

ክፍያው የሚሰበሰበው ፦

  • የስርዓት ማሻሻያዎችን ለመደጎም፣
  • የሳይበር ደህንነትን ለማሳደግ
  • የሐሰተኛና በብዛት የሚቀርቡ የተጭበረበሩ ማመልከቻዎችን ለመቀነስ ያለመ ነው።

የምዝገባው ጊዜ እንደተለመደው በተያዘዉ በጥቅምት ወር የሚጀምር ሲሆን፣ ክፍያው የሚፈጸመው በኦፊሴላዊው ድረ-ገጽ አማካኝነት በኤሌክትሮኒክ ካርዶች ብቻ መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

via_tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...