አሜሪካ ከፍልስጤም ድጋፍ ጋር በተያያዘ 300 የውጭ አገር ተማሪዎች ቪዛ ሰረዘች

Date:

ከፍልስጤም ድጋፍ ጋር በተያያዘ 300 የውጭ አገር ተማሪዎች ቪዛ መሰረዙን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ገለጹ።

በዩኒቨርስቲዎች ቅጥር ግቢ ለፍልስጤም የሚደረጉ የድጋፍ ሰልፎችን ለመግታት የትራምፕ አስተዳደር እየወሰዳቸው ካሉ እርምጃዎች አንዱ ነው ተብሏል።

“በዚህ ወቅት ከ300 በላይ ሊሆን ይችላል” ሲሉ ነው በጋያና ጉብኝታቸውን እያደረጉ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች የተናገሩት።

“ከእነዚህ ቀውሶች አንዱን ባገኘን ቁጥር ፤ በየቀኑ የምናደርገው ነን” ብለዋል።

አስተዳደራቸው ጸረ እስራኤል ነው የሚል ትርክት ከሚያራምድባቸው ዩኒቨርስቲዎች መካከል የምን ያህል ተማሪዎች ቪዛ እንደተሰረዘ ተጠይቀው ነው ይህንን ያሉት።

በቱፍትስ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ተማሪ ቱርካዊ ከቀናት በፊት በኢሚግሬሽን ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ሩቢዮ ይህንን ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብለዋል።

በተማሪዋ ላይ ክስ ስለመቅረቡ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።

ተማሪዋ ሉዊዚያና በሚገኝ የስደተኞች ማሰሪያ ማዕከል ተወስዳለች።

አንድ የፌደራል ዳኛ በማሳቹስተስ እንድትቆይ ውሳኔ ቢያስተላልፉም ነገር ግን ተማሪዋ በሉዊዚያና እንደምትገኝ የፌደራል መዛግብት ያሳያል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...