*በህንድ የአህመደዳብ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነር ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ፣ ከተከሰከሰው አውሮፕላን አንድም ሰው በህይወት የተረፈ እንደሌለ ቢናገሩም፣ አሁን ላይ ግን አንድ ሰው በህይወት መገኘቱን ለህንድ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል፡፡
*ከተረፉት ግለሰቦች አንዱ እንግሊዛዊ ሲሆን፤ ከአውሮፕላኑ ውስጥ በመስኮትበመዝለል በ”ተዓምር” ከሞት መትረፉ ተዘግቧል፡፡
“አውሮፕላኑ ከመሬት ከተነሳ 30 ሰከንዶች በኋላ ከባድ ድምጽ ተሰማ፤ ከዚያ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፤ ሁሉም ነገር በከፍተኛ ፍጥነት ነው የሆነው” – በህይወት የተረፈው እንግሊዛዊ
*በአውሮፕላኑ 169 ህንዳውያን፣53 እንግሊዛውያን፣ እንዲሁም 7 የፖርቱጋልና 1 የካናዳ ዜግነት ያላቸው ተሳፋሪዎች ነበሩ – የሕንድ አየር መንገድ
*የሟቾች ቁጥር 290 መድረሱ የተዘገበ ሲሆን፤ እስካሁን 204 አስከሬኖች መገኘታቸውን የፖሊስ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል – ነገር ግን አውሮፕላኑ ሲከሰከስ ምን ያህሎቹ መሬት ላይ ወይም በአውሮፕላኑ ውስጥ እንደነበሩ አይታወቅም ብለዋል፡፡
*አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሃኪሞች ማረፊያ ቤት ላይ ነው – አንዲት እናት ወንድ ልጇ እንዴት ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ዘሎ ህይወቱን እንዳተረፈ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጻለች፡፡
*የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በህንድ በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ ልባቸው መሰበሩን ገልጸው፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
