አዲስ የብቃት ማረጋገጫም ሆነ ነባር የብቃት ማረጋገጫ እድሳት እንዲሁም የጅቡቲ መግብያ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ለማግኘት በአካል መምጣት አያስፈልግም አለ የትራምስፓርትና ሌጂስቲክ ሚኒስቴር
ከሃምሌ 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በመሉ ወደ በዲጂታል ስርዓት መቀየሩን ይፋ ያደረገው የትራንስፓርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ፤ የኦፕሬተሮች የብቃት ማረጋገጫ ፣ የእድሳት አገልግሎት ነባር እድሳት፣ የጅቡቲ መግብያ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች በኦንላይን እየሰጠ መሆኑን አስታውሷል፡፡
ስለሆነም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲስ የብቃት ማረጋገጫም ሆነ ነባር የብቃት ማረጋገጫ እድሳት እንዲሁም የጅቡቲ መግብያ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ለማግኘት በአካል መምጣት እንደማያስፈልግ ገልፃል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያቤቱ አዲስ የብቃት ማረጋገጫም ሆነ ነባር የብቃት ማረጋገጫ እድሳት እንዲሁም የጅቡቲ መግብያ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ለማግኘት በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://iftms.motl.gov.et
በመመዝገብ አገልግሎቶቹን ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲያገኙም አሳስቧል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር!
