ኢራን የእስራኤል የስለላ ድርጅት ‘ሞሳድ’ ዋና መስሪያ ቤትን በሚሳኤል መምታቷ ተዘገበ

Date:

ኢራን የእስራኤል የስለላ ድርጅት ‘ሞሳድ’ ዋና መስሪያ ቤትን በሚሳኤል መምታቷን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ታስኒም የዜና ወኪል ዘገበ።

የዜና ወኪሉ የአገሪቱን አብዮታዊ ብሔራዊ ዘብ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የሞሳድ ቢሮ በኢራን ሚሳኤሎች መመታቱን ገልጿል።

ታስኒም የሞሳድ መስሪያ ቤት እንደሆኑ የገለጻቸው ህንጻው በእሳት ተያይዞ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አጋርቷል።

“የኢራን አብዮታዊ ብሔራዊ ዘብ የኤሮስፔስ ተዋጊዎች ከፍተኛ ውጤት ለማምጣት ባነጣጠረ ዘመቻ ምንም እንኳን ከፍተኛ የላቁ የመከላከያ ስርዓቶች ቢዘረጉም የወታደራዊ ስለላ ማዕከሉን መትተዋል” ሲል የዜና ወኪሉ በቴሌግራም ገጹ አጋርቷል።

እስራኤል በሞሳድ ላይ ስለተፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት ያለችው ነገር የለም።

የእስራኤል መንግሥት በጣለባቸው እገዳዎች ምክንያት አንዳንድ በጥቃቱ ኢላማ የተደረጉ ስፍራዎችን በተመለከተ የአገሪቱ ሚዲያዎች ሊዘግቡ አይችሉም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...