የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) የሀገሪቱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አቅም ይበልጥ ለማሳደግና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ያረፈባቸውን 100 አዳዲስ ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀምሯል።
የኢባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ በወቅቱ እንደተናገሩት፣ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ድርጅቱ ካሉት 556 ተሽከርካሪዎች ጋር ተዳምረው የጭነት ፍሰቱን ለማሳለጥና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለፁት፤ አሽከርካሪዎቹ የኢትዮጵያን ስም በድንበር ተሻጋሪ መንገዶች ላይ ከፍ ያደረጉ የኢኮኖሚ ጀግኖች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ በሀገር ፍቅርና በሙያ ስነ-ምግባር ተግተው ስራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ተሽከርካሪዎቹን ለአገልግሎት ብቁ በማድረግ ረገድ በቴክኒክና በጥገና ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የድርጅቱ ሰራተኞች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
