ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገር ለምታስገባው የምግብ ዘይት ከ650 ሚሊዮን ዶላር በላይ ታወጣለች

Date:

ዘይት አንዳንዴ ከ #ቀረጥ_ነፃ  አንዲገባ ሲፈቀድ፣ ከገበያ ሲጠፋ፣ ዋጋው ሲሰቀል በተደጋጋሚ ያጋጥማል፡፡

ለዚህ የምግብ ዘይት ችግር አንድ አማራጭ የሚሆን የምርመራ ውጤት የኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩ ተመራማሪዎች እንካችሁ ብለዋል፡፡

ምርምሩ በእጅ በሚሰራ አነስተኛ ማሽን ከ #አቮካዶ የምግብ ዘይት ማምረት ነው፡፡

ምርምሩን በውጤት እስኪታጀብ 3 ዓመታት መውሰዱን በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተማራማሪ እና የምርመራ ስራው አባል እዩቤል ሙሉጌታ ነግረውናል፡፡

አቮካዶ አምራች ገበሬዎች በየሰፈራቸው ተደራጅተው ከቁርጥራጭ ብረቶች በተሰራችና 50,000 ብር በምታወጣ ማሽን የምግብ ዘይት የማምረት ምርምር አመርቂ ውጤት አምጥቷል ተብሏል፡፡

በዚህም ከ100 ኪ.ግ የአቮካዶ ፍሬ 8 ሊትር ዘይት ማግኘት ችለናል ሲሉ ተመራማሪው አስረድተዋል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...