የሩሲያ ምክትል የኢነርጂ ሚኒስትር ሮማን ማርሻቪን በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ጅሩ ጋር በሀገራቱ የኃይል ልማት ትብብር ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት “በሰው ኃይል ስልጠና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲሁም የውኃ ምንጮችን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም እና አዳዲስ የኃይል አማራጮችን ለማሰስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነን” ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለቱ አካላት እ.አ.አ በ1988 በሶቪየት ሕብረት ባለሙያዎች የተገነባውን የመልካ ዋከና የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ለማዘመን በትኩረት መክረዋል። ሥራ ከጀመረ አንስቶ የደረጀ የመሳሪያ ጥገና ተደርጎለት የማያውቀው ጣቢያው በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው መሠረተ ልማቱ የማሻሻያ ሥራ እንደሚያስፈልገውም ተነስቷል።
በውይይቱ ላይ ሁለቱ ወገኖች ብሪክስን እና ዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጀንሲን ጨምሮ በባለ ብዝሃ ወገን መድረኮች ላይ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጎልበት ተስማምተዋል።
