የኢትዮጵያ መንግስት የቻይናው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል የካናዳውን አላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን በ4 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ያደረገውን ስምምነት በይፋ ማጽደቁን ካፒታል ከምንጮቹ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል።
በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፣ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ትልቁ ዘመናዊ የወርቅ ማውጫ ይሆናል።
በ620 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለው ማዕድኑ፣ በዓመት ወደ 290 ሺህ አውንስ ወርቅ የማምረት አቅም አለው። የኩባንያው የባለቤትነት መብት ቢቀየርም፣ ነባሩ የህግ እና የውል ማዕቀፍ እንደማይቀየር ተገልጿል ።
