ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችን ድጋፍ በይፋ ጠየቀች።
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን በዚሁ ጉዳይ ላይ በቅርቡ በሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ግንኙነት ዳይሬክተርና የባንኩ ተወካይ ከሆኑት ቱራዬያ አልሃሺሚ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅት አምባሳደር ዑመር ሁሴን ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ለመሆን ያላትን ፍላጎትና እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶች በዝርዝር ገልጸዋል። በተለይም ኢትዮጵያ ለተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ያላትን ወዳጅነት በመጥቀስ ለአባልነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጡላቸው ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ኤምባሲም ይህንኑ መረጃ አረጋግጧል።
የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ራሷ እ.አ.አ ጥቅምት 4 ቀን 2021 የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን መቀላቀሏ አይዘነጋም።
