ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከለማ እንቁላል ሽያጭ ከ1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች ተባለ

Date:

ኢትዮጵያ በ2017 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት የተለያዩ የእንስሳት ምርቶችን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ችላለች ሲል የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አስራት ጤራ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለአለም ገበያ ከምታቀርባቸው የእንስሳት ምርቶች መካከል የለማ እንቁላል ተጠቃሽ ነው።

አያይዘውም በአሁኑ ወቅት ላይ ምርቱን  ወደ ተለያዩ የአለም ሀገራት ለሽያጭ እያቀረበች እንደምትገኝ ገልፀዋል።በዚህም መሰረት ባለፋት ዘጠኝ ወራት 235 ቶን የለማ እንቁላል ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ መደረጉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረው በምላሹ  1 ነጥብ 41 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል ።

የለማ እንቁላል በአሁኑ ወቅት AGP poultry በተባለው ድርጅት አማካኝነት ለውጪ ገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል።ከምርቱ ተቀባይ ሀገራት መካከል ዮጋንዳ ከፍተኛውን ድርሻ መያዟ ሲነገር ኮትዲቯር፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ጋና እና ማዳጋስካር እንደየቅደም ተከተላቸው የምርቱ ዋንኛ ተቀባይ ሀገራት ናቸዉ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...