ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል የሚውል የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር ወይም የ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ተፈራርመዋል፡፡

ከተፈረመው ስምምነት ውስጥ 50 ሚሊየን ዶላሩ ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በብድር መልክ የተሰጠ ሲሆን÷ 46 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ከዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ፈንድ በድጋፍ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ድጋፉ የቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ የሚውል ነው መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ደረጃ ያሉ መምህራንን አቅም ለመገንባት እንዲሁም ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር በተጣጣመ መልኩ የቅደመ መምህርነት ስልጠናዎችን ለመስጠት እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም ለማጎልበት፣ የሴት አመራሮችን ለመደገፍ እና በዲጂታል የታገዘ ሥርዓት ትምህርትን ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑ ተጠቅሷል፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...