በሮም በተካሄደ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የጣሊያን የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር ጂያንካርሎ ጆርጌቲ የሁለትዮሽ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለመደገፍና የውጭ ዕዳ ጫናን ለመቀነስ ያለመ ሲሆን፣ በጣሊያን በኩል ደግሞ አገሪቱ ከአፍሪካ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር የነደፈችው የ”ማቲ ዕቅድ” አካል ነው ተብሏል።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የጀመረችው የዕዳ አያያዝ ሂደት ውጤታማ መሆኑን የሚያሳይና ለቀጣይ የኢኮኖሚ ማገገሚያ ስራዎች ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።
