ኢትዮጵያዊቷ ሴት መካኒክ የተባበሩት መንግሥታት የክብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኑ

Date:

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ በመካኒክነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ሻለቃ ትዕግስት ፈረደ፤ በተለምዶ የወንድ ሥራ ተብሎ በሚቆጠረው ሙያ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ የክብር ሜዳሊያ ተሸልመዋል።

በምዕራብ ኢኳቶሪያ (ያምቢዮ) በተሠማራው የኢትዮጵያ ሰላም አሰከባሪ ኃይል አባል የሆኑት ሻለቃ ትዕግስት፤ የሰላም አስከባሪ ተሽከርካሪዎች ሁልጊዜ ለተልዕኮ ዝግጁ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና በመጫወታቸው ነው እውቅናውን ያገኙት፡፡

“ሁሉም የምጠግናቸው ተሽከርካሪዎች ተስፋን ይሰንቃሉ። ደህንነታቸው ተጠብቆ ሲንቀሳቀሱ ለሰላም የበኩሌን እንደተወጣሁ ይሰማኛል። ይህንን ሜዳሊያ በማጥለቄ በሰላም ማስከበር ሥራ ውስጥ ትንሽ የሚባል ሚና እንደሌለ ተገንዝቤያለሁ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን ከደቡብ ሱዳን በፊት የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኳቸውን በሱዳን ተወጥተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...