ኤሎን መስክ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስርቻለሁ አለ።
መስክ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ከገባ በኃላ “አሜሪካ ፓርቲ” የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋሙ ተነግሯል።
ቱጃሩ መስክ ያቋቋመው ፓርቲ፤ በአሜሪካ የሪፐብሊካን እና ዲሞክራት የሁለት ፓርቲ ስርዓትን ለመገዳደር ያለመ ስለመሆኑ በኤክስ ገፁ አስታውቋል።
ሆኖም ፓርቲው በይፋ በአሜሪካ የምርጫ አስፈፃሚ አካላት መመዝገቡ እንዳልታወቀ ቢቢሲ ዘግቧል።
ከአሜሪካ ሀገር ውጭ እንደተወለደ የሚነገርለት መስክ፤ በዚህ ምክንያት በአሜሪካ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ባይችልም ፓርቲውን ማን እንደሚመራው አልተናገረም።
መስክ ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን አዲስ የግብር ቅነሳ እና የብሔራዊ ደህንነትን ያጠነክራል ያሉትን ህግ የተቃወመ ሲሆን፤ ህጉ ከጸደቀ ፓርቲ እንደሚመሰርት መግለፁ ይታወሳል።
