መገኛው በትግራይ ክልል ሓውዜን ከተማ ያደረገው ፍረ ሰማእታት አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ከአንዲት እናት ሆድ 8.9 ኪሎግራም የሚመዘን እብጠት በቀዶ ህክምና ማስወገድ መቻሉን ቀዶ ህክምናውን የሰራውና የሆስፒታሉ ባልደረባ የሆነው ተክለማርያም ተስፋማርያም ተናግረዋል።
እንደ ሞያተኛው ገለፃ ከሆነ ቀዶ ህክምናው የተደረገላት እናት የ32 ዓመት ሴት ስትሆን ከቆራሮ ጤና ጣብያ በሪፈር የመጣች ነች ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም እብጠቱ ለአስር ዓመታት ያህል በሆዷ የቆየ መሆኑም ተገልፆል።
ወጣቷ ቀዶ ህክምናው በምታደርገበት ወቅት የሶስት ወር ነፍሰጡር የነበረችም ሲሆን ከቀዶ ህክምናናው በኃላም ፅንሱ በጥሩ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ተብሏል።
የቀዶ ህክምናው ሂደቱ ለ3 ሰዓታት ያህል የዘለቀ ነበር የተባለ ሲሆን በቀዶ ህክምናው የተወገደው እብጠት ለተጨማሪ የካንሰር ምርመራ ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተልኮ በምርመራ ውጤቱም ከካንሰር ነፃ መሆኑ መረጋገጡን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
