የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲን በሀላፊነት መቅጠሩን በይፋ አስታውቋል።
የብራዚል እግርኳስ ፌዴሬሽን በመግለጫው “ በታሪክ ትልቁ ብሔራዊ ቡድን በአለም ስኬታማው አሰልጣኝ ይሰለጥናል ” ሲል አስተዋውቋል።
ካርሎ አንቾሎቲ የብራዚል ብሔራዊ ቡድንን እስከ 2026 አለም ዋንጫ እንደሚመሩ ተገልጿል።
የብራዚል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኤድላንዶ ሮድሪጉዌዝ በሰጡት አስተያየት “ አንቾሎቲን መሾም ስልታዊ እርምጃ ነው ብለዋል።
አክለውም ” ውሳኔው ብራዚል ያጣችውን የመሪነት ስፍራ ለማስመለስ መቁረጣችንን ለአለም ያሳየ ነው “ ብለዋል።
