በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ በድምጻዊነቷ እንዲሁም በግጥምና ዜማ፣ በትወና ችሎታዋ ከፍተኛ ስምን ያተረፈችውና በኋላም ሙሉ ጊዜዋን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ወደ ዝማሬ ዓለም የገባችው አርቲስት ዘሪቱ ከበደ “ከልጅነት እስከ ልጁነት” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ጽፋ በቅርቡ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።
በግል ታሪኳ ላይ የሚያጠነጥነው ይህ መጽሐፏ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል።
ከሰሞኑም የመጽሐፏ ጉዳይ በሁለት ጉራ ከፍሎ ሲያወያይ፣ ሲያከራከርም ተመልክተናል።
አርቲስት ዘሪቱ ከበደ በዚህ መጽሐፏ ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት ዛሬ ቀጠሮ ይዛለች።
ይህ ቀጠሮ በነገረ መጽሃፍት አዘጋጆች በኩል የተሰናዶ ሲሆን ቅዳሜ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቀበና በሚገኘው Fss አዳራሽ ውስጥም ይከናወናልም ተብሏል።
የዝግጅቱ አቅራቢና አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እንደሆነም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
