የህወሓት ህጋዊ ሰውነት እንዲመለስለት የፓርቲው አመራሮች ጠየቁ

Date:

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ጎራ መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች፤ ፓርቲው ዳግም ምዝገባ እንዲያካሄድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን ትእዛዝ በመኮንን፤ ህጋዊ ሰውነቱ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እንዲመለስለት ጠየቁ። እነዚሁ አመራሮች በክልሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትን ያቀፈውን የጊዜያዊ ምክር ቤት ህልውና እንደማይቀበሉትም አስታውቀዋል።

የፓርቲው አመራሮች ይህን ያስታወቁት፤ ከሐሙስ ሚያዝያ 23 ጀምሮ በመቐለ ከተማ በሚገኘው የሰማእታት ሃውልት አዳራሽ ሲያካሄዱት የቆዩትን ስብሰባ በትላንትናው ዕለት ሲያጠናቀቁ ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ ነው። “ብሔራዊ አንድነታችን ሉአላዊነታችን ለማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ስብሰባ፤ 1,337 የፓርቲው መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል ተብሏል።

የስብሰባው ተሳታፊዎች በስብሰባቸው ማጠቃለያ ባወጡት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የህወሓት የህጋዊ ሰውነት የማግኘት ጉዳይ ነው። ህወሓት 50 ዓመት የሞላው እና “በህዝቡ ልብ የታተመ” መሆኑን በመግለጫቸው የጠቆሙት አመራሮቹ፤ የፓርቲው እውቅና “በትግራይ ህዝብ የሚወሰን ነው ብለን እናምናለን” ሲሉ አቋማቸውን አስታውቀዋል።

ከፕሪቶሪያ ስምምነት በተቃራኒ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በድጋሚ ለመመዝገብ የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ሙከራ እንደሚያወግዙም አመራሮቹ በአቋም መግለጫቸው ላይ አስፍረዋል።

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15799/

@EthiopiaInsiderNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...