ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ከኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት መንግሥታቸው አለመግባባቶችን ለመፍታት ኃይልን መጠቀም እንደማይቀበል እና ልዩነቶችን ለመፍታት ውይይት መሠረት ሊሆን እንደሚገባ አጽዕኖት ሰጥተዋል ሲል የሳዑዲ የዜና ወኪል ዘግቧል።
እንደ ሚዲያው ዘገባ ከሆነ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ልዑል አልጋ ወራሹ ለኢራን እና ለኢራን ሕዝብ ላሳዩት መልካም ስሜት በማመስገን፤ መንግሥታቸው የእስራኤልን ጥቃት በመቃወም እና በማውገዝ ረገድ የያዘውን አቋም አድንቀዋል።
የኳታር አሚር ታሚም ቢን ሀማድ አል ታኒም ከኢራን ፕሬዝዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት የእስራኤልን ጥቃት ያወገዙና ለኢራን አመራር ድጋፍ የሰጡ የመጀመሪያው የአረብ መሪ ሆነዋል ሲል ስለተፈጠረው ስፑትኒክ ዘግቧል ።
