“ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶአን ከሶሪያው ፕሬዝዳንት አሕመድ አል-ሻራ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል።
መሪዎቹ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ስላለው ግጭት እንዲሁም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ኤርዶአን እስራኤል የለኮሰችው ተንኳሽ ጥቃት ቀጣናውን ያሰጋ እንደሆነ ጠቁመው፤ ሶሪያ ከዚህ ግጭት መራቅ እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተዋል” ሲል የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።
መግለጫው አክሎም ኤርዶአን የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ አሸባሪ ድርጅቶች እና ጽንፈኛ አካላትን መጠንቀቅ አስፈላጊ መሆኑንም አጉልተው አስረድተዋል ተብሏል።
