የምርጫ ቦርድ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ውይይት ተደረገ

Date:



የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከምክር ቤቱ የህግ ክፍል እና ከምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል።


ቋሚ ኮሚቴው፣ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ያደረገውን ጥረት አድንቋል።


በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደት እራሳቸውን እየቻሉ እንዲሄዱ ለማስቻል ከአባሎቻቸው 30 በመቶ መዋጮ እንዲሰበስቡ የሚያስገድደው ድንጋጌ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴው ከምርጫ ጊዜ ባሻገር ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የሚደረገው ጥረት የሚመሰገን መሆኑን አንስቷል።


ኢትዮጵያ በልምምድ ላይ ያለ ዲሞክራሲ እንዳላት የጠቆመው ቋሚ ኮሚቴው፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል ለሚፈጠሩ ስህተቶች ከማሰረዝ ይልቅ ደረጃ በደረጃ እያረሙና እያስተማሩ መሄድ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደሚያሰፋና የፓርቲዎቹንም በጎ አስተዋጽኦ ከፍ እንደሚያደርግ አሳስቧል።


በተጨማሪም ምርጫን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በሂደት ለመለማመድ መታሰቡ ወቅታዊና ተገቢ መሆኑን የገለጸው ቋሚ ኮሚቴው፣ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ሲመሰረቱ ነዋሪነታቸው በሰባት ክልሎች የሆኑ አባላት እንዲኖራቸው የሚለው ሀሳብም ፓርቲዎቹ ሀገራዊ ገጽታ እንዲላበሱ እንደሚያደርግ አመላክቷል።


የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ በበኩላቸው፣ ምርጫ ቦርድ ከአለም አቀፍ ልምዶች በተጨማሪ የራሱን ተሞክሮ ተጠቅሞ ያቀረበው የማሻሻያ አዋጅ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። ረቂቅ አዋጁ ዘመናዊ ምርጫ እንዲኖርና የዜጎችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ፣ በተለይም የሴቶችንና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማካተት የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑንም አክለዋል።


በረቂቅ አዋጁ ከተካተቱ ማሻሻያዎች መካከል፣ አንድ ግለሰብ ለመምረጥና ለመመረጥ የነበረው የ18 እና የ21 ዓመት የዕድሜ ገደብ የምርጫ ምዝገባ ቀንን ሳይሆን የምርጫ ቀንን መሰረት እንዲያደርግ ሆኖ መስተካከሉን ያብራሩት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላት ወርቀሃይሉ ናቸው።


ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ምርጫ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጊዜ ለማካሄድ እንደማይታሰብ የገለጹት ሰብሳቢዋ፣ ነገር ግን በተቻለ አቅም በቴክኖሎጂ የታገዘ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት መኖሩንና በቀጣይም የሽፋን መጠኑን ማስፋት እንደሚቻልም ነው የተቆሙት።


ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መስራች አባላት ከሰባት ክልሎች እንዲሆኑ የተደረገበት ምክንያት ያስረዱት የቦርዱ የህግ ክፍል ኃላፊ ወይዘሮ መነን አበበ፣ ቀድሞ የነበረው የአራት ክልሎች ገደብ አሁን ካለው የክልሎች ቁጥር መጨመር ጋር እንዲጣጣም መደረጉን ገልጸዋል።


በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለድርሻ አካላትና ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር ተጨማሪ ውይይት እንደሚደረግ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።የምርጫ ቦርድ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ውይይት ተደረገ
NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...