▪️ ዛሬ ጠዋት የዩክሬን ልዑካን ከአሜሪካ እና ቱርክ ተወካዮች ጋር በኢስታንቡል ተወያይተዋል።
▪️የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ቀጥሎ የተደረገው ውይይት ለጋዜጠኞች ዝግ ነበር።
▪️ ድርድሩ ለሁለት ሰዓታት ያህል ቆይቷል።
▪️ከድርድሩ መጠናቀቅ በኋላ የሩሲያ ዋና ተደራዳሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ መግለጫ ሰጥተዋል።
▪️የሩሲያ ልዑካን በድርድሩ ውጤት አጥጋቢ እንደነበር ፣ 1 ሺህ የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ እንደ ተስማሙ እንዲሁም ሞስኮ ንግግሩን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ዋና ተደራዳሪው አጽንኦት ሰጥተዋል።
▪️ከድርድሩ በኋላ ዜለንስኪ፣ ማክሮን፣ ሜርዝ፣ ስታርመር እና ቱስክ ከትራምፕ ጋር ተነጋግረዋል።
▪️ ትራምፕ ዛሬ ምሽት የዩክሬንን የሰላም ጉዳይ ለመወያየት ለፑቲን ሊደውሉ እንደሚችሉ አሳዉቀዋል።
▪️የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደገለጹት በፑቲን እና ትራምፕ መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች ሰላምን ለማምጣት እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
▪️የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን ሌላ ዙር ስብሰባ ለማድረግ መሰረታዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
