የሩስያ እና ቻይና መሪዎች ያልተገኙበት የብሪክስ አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ተጀመረ

Date:

ለሁለት ቀናት ይቆያል በተባለው ጉባኤው ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ምላሽ መስጠትን ጨምሮ በዋና ዋና የጥምረቱ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

ብራዚል የወቅቱ ፕሬዚዳንት በሆነችበት የጥምረቱ ጉባኤ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ቺንፒንግ አለመገኘታቸው ተዘግቧል።

ይህም የፕሬዚዳንቱ በጉባኤው አለመገኘት ብሪክስ ከተመሰረተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንም እንዲሁ በጉባኤው ያልተገኙ ሲሆን ምክንያታቸው ደግሞ በዩክሬን ላይ ወረራ ፈጽመዋል በሚል በዓለማቀፉ የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት የክስ ማዘዣ ዋራንት ወጥቶባቸው ስለነበር ነው ተብሏል።

ጉባኤተኛው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተከተሉት ጠንካራ የቀረጥ ፖሊሲ አቋማቸውን በአንድነት ለመግለጽ መዘጋጀታቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዲ ፒ ኤ ዘግቧል።

ጉባኤው በተጨማሪ የጤና ፖሊሲ ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዓለማቀፍ የአየር ንብረት ጥበቃ በዋነናነት ትኩረት እንደሚሰጡበት ነው የሚጠበቀው።

ብራዚል ፣ ሩስያ ፣ ህንድ ፣ ቻይና ፣ እና ደቡብ አፍሪቃ በጥምረት የመሰረቱት እና በኋላም ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ፣ የተቀላቀሉበት ጥምረቱ 48 በመቶ የዓለማችን የህዝብ ቁጥር እና 24 ከመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ እንደሚይዙ ዘገባው አመልክቷል።

የብሪክስ አባል ሃገራት ጥምረት በኤኬኖሚ የበለጸጉ የቡድን ሰባት አባል ሃገራትን ለመገዳደር የተመሰረተ ጥምረት ነው።

በጉባኤው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የተቀሩ የጥምረቱ ሃገራት መሪዎች እና ተወካዮች ታድመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...