የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

Date:

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ አዲስ ከፍተኛ ኃላፊነት ተሰጣቸው።

ፕሬዝደንቷ የተመደቡት በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ ውስጥ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ እንዲያደርጉ ሲሆን፣ ዋና ተግባራቸውም ተቋሙ ለአካባቢው ቀውሶች በሚሰጠው ዘገምተኛ ምላሽ ሳቢያ የሚነሱበትን ትችቶችና የአሰራር ክፍተቶች መመርመር ነው።

ይህንን ከባድ አህጉራዊ አደራ ለመወጣት የያዝነው የሰኔ ወር እንደተጠናቀቀ በቀጥታ ወደ ስራ ይገባሉ።

ወይዘሮ ሳህለወርቅ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት በመጀመሪያ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ የሚቀበሉ ሲሆን፣ በመቀጠልም የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ወደ ሚገኝበት ሴኔጋል ዳካር በመጓዝ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያሉ።

ለቀድሞዋ ፕሬዝደንት ይህ ታላቅ ኃላፊነት ሊሰጣቸው የቻለው ቀደም ሲል በሴኔጋል፣ ማሊ፣ ጊኒና ኬፕ ቨርዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ባገለገሉበት ወቅት ስለ ቀጠናው ባካበቱት የላቀ እውቀትና ሰፊ ግንዛቤ መሆኑ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...

አሜሪካ እና እስራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለአገሪቱ ጦር የማስረከብ ዕቅድ

አሜሪካ ድጋፏን በሰጠችው ዕቅድ መሠረት እስራኤል እና ሊባኖስ፤ የደቡብ...