የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ

Date:



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ መደበኛ ያልሆኑ አሰራሮችን ለመግታት የ2019 በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ እንዲጸድቅ መወሰኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት የተወሰነ ሲሆን፣ በከተማዋ የተካሄደ ሳይንሳዊ ጥናትንና የነዋሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆኑ ተገልጿል።

ውሳኔው አከራዮች ወቅታዊውን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ተከራዮች ደግሞ ካልተገባ የዋጋ ጭማሪና መፈናቀል ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ምዝገባና የውል እድሳት ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች በይፋ መጀመሩ ቢሮው አያይዞ ገልጿል።

” ይህ አሰራር በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው ” ብሏል።

ቲክ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

ላለፉት 5 አስቸጋሪና ፈታኝ ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም)...

ንባብ ለሕይወት  እየመጣ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

“ወጣቱን በጉልበት እያፈሱ ወደ ጦርነት እየነዱት ነው!”

"ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት በትግራይ፦ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበረሰብ አንቂዎች...