የታሸጉ ምግብ-ነክ ምርቶች ላይ የኮሊስትሮል፣ የጨው እና ስኳር መጠንን ጨምሮ ሌሎች ግብዓቶችን ደረጃ የሚወስን አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ለስኳር፣ ለደም ግፊት፣ ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት እና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የማጋለጥ እድል ያላቸውን የታሸጉ የፋብሪካ ምግቦች ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ አዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለማቅረብ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

መመሪያው የሕግ ሂደቶችን አልፎ በዚህ ዓመት መጨረሻ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል ተብሏል።

የመመሪያው ዓላማ፤ በፋብሪካ የዝግጅት ሂደት አልፈው ለሕብረተሰቡ የሚቀርቡ የምግብ ምርቶች ውስጣቸው ያለውን የንጥረ ነገር ይዘትና መጠን በግልጽ በምግቡ ማሸጊያ ላይ እንዲያስቀምጡ ማስገደድ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በምግብ ይዘታቸው ላይ ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ቅመሞች ከመጠን በላይ የያዙ ምርቶች በማሸጊያቸው ላይ የጤና ማስጠንቀቂያ እንዲለጥፉ በማድረግ ሕብረተሰቡ ስለምግቡ ምንነት በቂ እና እውነተኛ መረጃ እንዲኖረው የማስቻል ዓላማን መያዙ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ሌሊሳ አማኑኤል፤ “በኢትዮጵያ በተለይም በአመጋገብ ችግር እና በተሳሳተ የኑሮ ዘይቤ ምክንያት በሚከሰቱ በሽታዎች የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው” ብለዋል።

ከመንገድ ላይ የተጠበሱ ምግቦች ጀምሮ በፋብሪካ ተቀነባብረው እስከሚወጡ ምርቶች ድረስ ያሉ ምግቦችን፤ የቅባት፣ የጨው፣ የስኳር፣ የተለወጠ ስብ (ትራንስ ፋት)፣ የኮሊስትሮል እና መሰል በጥንቃቄ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ምግቦች ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።

ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት የሚከሰቱ ሕመሞችን እና የሚያጋጥምን የሞት መጠን ለመቀነስ፤ ሀገር ለመድኃኒት አቅርቦትና ለሕክምና አገልግሎት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማዳን የፋብሪካ ምርቶች የንጥረ-ነገር ቁጥጥር ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ አማካሪው አቶ ሌሊሳ ተናግረዋል።

አሐዱ ሬዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...