የአሜሪካ መንግስት ለሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የ60 ሚሊዮን ዶላር አቋረጠ

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (ኤች ኤች ኤስ) ለሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የፌደራል ዕርዳታ 60 ሚሊዮን ዶላር እያቋረጠ መሆኑን ገልጿል፣ ይህም በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር እና በዩኒቨርሲቲዉ መካከል በፀረ ሴማዊነት፣ በፕሬዝዳንታዊ ቁጥጥር እና በአካዳሚክ ነፃነት ወሰን መካከል ያለውን ፍጥጫ ይበልጥ እያባባሰ እንደሚሄድ ይጠበቃል

“የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፀረ-ሴማዊ ትንኮሳን እና የዘር መድሎዎችን ለመፍታት ባለመቻሉ የበርካታ ዓመታት የድጎማ ሂደት ይቋረጣል፡፡ ይህም በአጠቃላይ ወደ 60 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ መሆኑን” መምሪያው በኤክስ ላይ አስታዉቋል።በዩኒቨርሲቲ ግቢው ውስጥ መድልዎ “አይታገስም” ፣ “የፌዴራል ፈንድ ሁሉንም ተማሪዎች የሚጠብቁ ተቋማትን መደገፍ አለበት” ብሏል።

የትራምፕ አስተዳደር ለሀርቫርድ በፌዴራል የሚሰጠውን ከ2.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አግዷል።የትምህርት ዲፓርትመንት ፀሐፊ ሊንዳ ማክማሆንም በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ዩኒቨርሲቲው ለከፍተኛ ትምህርት ለምርምር የህዝብ ገንዘብ እንደማይቀበል ለሃርቫርድ በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል።”ሃርቫርድ በህዝብ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ተቋም መሆኑ ያቆማል፣ እና በምትኩ በግል የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ተቋም ሆኖ መስራት ይችላል፣ ትልቅ ስጦታውን በመጠቀም እና ከሀብታም የቀድሞ ተማሪዎች ገንዘብ መሰብሰብ ይችላል” ሲሉ ማክ ማሆን አክለዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...