የአሸናፊ ግርማ የእግር ኳስ ህይወት የሚዳስስ መፅሐፍ ተመርቋል

Date:

የአሸናፊእግር ኳስ ኮከብ ህይወት የሚዳስስ መፅሐፍ ተመርቋል:

የቀድሞዉ የኢትዮጲያ ቡና እና የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ኮከብ፣ አሸናፊ ግርማን የእግር ኳስ ህይወት የሚዳስስና ከአሸዋ ሜዳ እሰከ አርጀንቲና+ ካናዳ የተሰኘ መጽሐፍ በዴሎፖል ሆቴል ተመርቋል።

ይሄ የተጨዋቹን የእግር ኳስ ጉዞ የሚዳስስ መጻፍ፣ በርካታ የስራ ኃላፊዎችና የስፖርት ቤተሰቦች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።

በምረቃዉ ወቅት የመጽሐፉን የዳሰሳ ጽሑፍ ያቀረበዉ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበብ በለጠ፣ አሸናፊ በመጸሐፍ ስለራሱ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ስፖርት ታሪክን በተለይም ከድሬደዋ የወጡ የስፖርት ሰዎችን በውብ ትረካ እንደሚቀርብ ገልጿል።

መጸሐፍን አጠናቆ ለንባብ እንዲያበቃ ለረዱት፣ በእግር ኳስ ህይወቱ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ እገዛን ለደረጉለት አሰልጣኞችና የስፖርት ቤተሰቦች ልባዊ ምስጋናዉን አቅርቧል። በዚህምበእሱ የእግር ኳስ በህይወት ዉስጥ ቁልፍ ሚና ለነበራቸዉ በህይወት ላሉትና ላለፉት ታላላቅ የስፖርቱ ባለዉለታዎች የምስጋና እዉቅና ስጦታ ተበርክቷል።

የመጻሐፉ ባለቤት አሸናፊ ግርማ፣ መጸሐፉን የጻፈበት ዋና ዓላማ መጭዉ ትዉልድ ከሱ ስኬትና ዉጣዉረዶች ልምድ አሳቦ መሆኑን ተናግሯል።

በቀጣይም አሁን በካናዳ እየሰራበት ያለሁን የታዳጊዎች ፕሮጀክት ለሚወዳትና በእግር ኳስ ብዙ ላበረካተላት ሀገሩ አስተዋጾ ለማበርከትና የታዳጊዎች ፕሮጀክትን ለመጀመር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጿል።

መፅሀፉ 300 ገጾች ያሉትና ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ተፅፎ ለአንባቢያን በቅቶ እንደነበረና አሁን የአሸናፊን የካናዳ የታዳጊዎች አሰልጣኝነት ህይወት እንደተጨመረበት እንዲሁም በ500 ብር ለሽያጭ መቅረቡ መገለጹ አይዘነጋም።

አምባሳደር ፍፁም አረጋ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁንን ጨምሮ፣ ኢንስትራክተር ሰዉነት ቢሻዉ፣ ኢንስትራክተር አብረሃም መብራቱ እንዲሁ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች በመጽሐፉ ምረቃ በዓሉ ላይ መታደም ችለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ የሴራሚክ ምርቶች በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ

ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier...

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...