የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበጀት ዓመቱ ከ9 ሺህ በላይ ህገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶች  ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

Date:

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ከዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ገምግሟል፡፡

በበጀት ዓመቱ ህገ-ወጥ ንግድን በመከላከልና በመቆጣጠር ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ሰፊ ስራ መሰራቱን የተገለጸ ሲሆን  በ68 ሺ 3 መቶ 33 የንግድ ድርጅቶች ላይ የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አራት  በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው የተገኙ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተሰምቷል፡፡

የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ተጋላጭነት ለመቀነስ የእሁድ ገበያዎችን ቁጥር ወደ 24 ማሳደግ መቻሉን ተጠቁሟል።  በገበያዎቹ ላይ የሚቀርቡ መሰረታዊ የግብርና እና ኢንዱስትሪ በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት እንዲቀርቡ የተሻለ ክትትልና ቁጥጥር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

አክለው በበጀት ዓመቱ የነበረውን ጥንካሬ ይበልጥ በማጠናከር እና እንደ ውስንነት የተነሱ ጉዳዮችን በማረም በቀጣይ በጀት ዓመት የበለጠ ውጤታማ ስራ ለመስራት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

bisrat radio

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...