የአዲስ አበባ የገቢዎች በስምንት ወር 145.9 ቢሊዮን ብር ሰበሰበ

Date:

በ2017 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 230.4 ቢሊየን ብረ ለመሰብሰቅ አቅዶ ወደ ስራ የገባው ቢሮው ይህንን እቅዱ ለማሳካትም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ቆይቷል። በተለይም ከገቢ አሰባሰብ ጋር በተያያዘ ያሉትን ችግሮች በመለየት ለመፍታት ጥረት ተደርጓል የተባለ ሲሆን በዋነኛትም ከአሰራር፣ ከአደረጃጀትና ቴክኖሎጂን አጠቃቀም ብሎም ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን በመለየት ለመፍታት የተለያዩ ስትራቴጂዎች መተግበራቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ  የኮሙኒኬሽን ክፍል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ቢሮው ባለፉት ስምንት ወራት 116.5 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ኪዚህም 113.7 ቢልዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን የገለት አቶ ሰውነት ይህም የእቅዱን 97.59 በመቶ ያሳካ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ እንደ መሬት ልማት አስተዳደርና የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቁጥጥር የመሳሰሉ በማዕከል ገቢ የሚሰበስቡ ተቋማት ደግሞ በስምንት ወሩ 37.9 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደው ሲሰሩ የነበሩት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 31 ቢልዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዳቸውን 81.7 በመቶ አሳክተዋል።

ሌሎች በክፈኮፍለ ከተማ ደረጃ ገቢ የሚሰበሰቡት እንደ የማዘጋጃ ቤት ያሉት ደግሞ ባለፉት ስምንት ወራት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረው 1.4 ቢልዮን ብር ሲሆን 1.2 ቢልዮን ብር ተሰብስቧል ይህም የእቅዱን 90.8 በመቶ ያሳካ ነው። በአጠቃላይ የአዲስ አበባ ከተማ የገቢዎች ቢሮ በስምንት ወር ውስጥ የእቅዱን 93.6 በመቶ ያሳካ መሆኑን አክለዋል።

ከዚህ ባለፈ ቢሮው የገቢ መሰረትን ለማስፋት፣ የእዳ ክትትልን አቅምን ለማሳደግ የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን ለይቶ ወደ ተግባር ገብቷል ያሉ ሲሆን ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ በተለይም ከኦዲት ጥራት ጋር ተያያዞ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የኦዲት ጥራት የሚያረጋግጥ የስራ ክፍልን በማደረጃት ወደ ስራ መገባቱን አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...