የአዲስ አበባ ፖሊስ ከባድ ወንጀሎችን በ45 በመቶ መቀነስ መቻሉን አስታወቀ

Date:

  

አሁናዊ የአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ መልካም የሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራ፣ በትራፊክ አደጋ ምርመራ እንዲሁም በተለያዩ የአስተዳደር ስራዎች፣ በሰው ሀብት እና በቴክኖሎጂ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በመስራት 65 በመቶ የከባድ ወንጀል ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን 45 በመቶ ከባድ ወንጀሎችን መቀነስ መቻሉን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። በተጨማሪም ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን የስራ ትስስር ከፍ ለማድረግ እና ተደራሽነቱን ለመጨመር በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም አክለዋል።

ወንጀል እንዲፈፀም ምክንያት የሆኑ ተብለው የታሰቡ ቦታዎች ማለትም ሺሻ ቤቶች ፣ ጫት ማስቃሚያ ቦታዎችና አደንዛዥ እፅ በሚያዘዋውሩ ሰዎች ላይ ጠንካራ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለወንጀል መቀነስ ምክኒያቶች በተለያዩ ቦታዎች ላይ በቀን እና በማታ ያሉ ፍተሻዎች እና የሲሲቲቪ ካሜራዎች አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው። በከተማይቱ 916 የሚሆኑ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ካሜራዎች እንዳሉ እና የወንጀል መከላከል ስራ ለመስራት እንደሚያግዙ ገልፀው በተጨማሪ በከተማዋ በተጠኑ መንገዶች ላይ 400 ካሜራዎች መገጠማቸውን ገልፀዋል።

አያይዘውም በከተማይቱ ከዘጠና በላይ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዳሉና አካባቢያቸውን እና ግቢያቸውን በሲሲቲቪ ካሜራ እንዲቆጣጠሩ እና የፖሊስ እና የተጠርጣሪ ግንኙነት ምን ይመስላል ሚለውን እና በአግባቡ እየተስተናገደ ነው የሚለውን ጭምር ለመከታተል እንደሚያስችል ገልፀዋል።

በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ የፖሊስ አባላት ላይ ከስነምግባር ጀምሮ በወንጀል እስከመጠየቅ ድረስ ጥብቅ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...