የአፍሪካ ሃገራት A7 የተሰኘውን የፋይናንስ መድረክ እንዲቀላቀሉ ተጠየቀ

Date:

ላቭሮቭ የንግድ መረጋጋትና ኢንቨስትመንትን ለመጠበቅ ያስችላል ያሉትን ይህንን የፋይናንስ መተግበሪያ አፍሪካውያን አጋሮች እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል።

ከአፍሪካ እስካሁን በሩሲያ የተመሰረተውን የፋይናንስ መድረክ ናይጄሪያ እና ዚምባቡዌ ተቀላቅለውታል።

ላቭሮቭ በብሔራዊ የሃገራት መገበያያ ገንዘቦች ንግድ ለማድረግ የሚያስችል መንገድ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ላቭሮቭ ሩሲያ በ2024 ይፋ ያደረገችው የA7 መድረክ የሩሲያ ቢዝነሶች በየትኛውም መገበያያ ገንዘብና ሃገር የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ ያስችላል ያሉ ሲሆን በሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል የሚፈፀሙ የጋራ ንግዶችም 84% መድረሳቸው ተነግሯል።

A7 የተሰኘው ድርጅት በሩሲያ የመከላከያ ዘርፍ ላይ ትኩረት በሚያደርገው PSB ባንክ የተመሰረተ ሲሆን የሩሲያን የአለም አቀፍ ንግድ ለማቀላጠፍ በማሰብ የተመሰረተ ነው።

ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የተነሳ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት ስዊፍት የታገደች ሲሆን አለም አቀፍ ንግዶችንም በእገዳው ምክንያት ማከናውን ከብዷታል።

A7 ለዚህ እገዳ አማራጭ በመሆን ሩሲያ በተለያዩ ሃገራት መገበያያ ገንዘብ የአለም አቀፍ ንግድን እንድታከናውን ሲያስችላት የአውሮፓ ህብረትም ከህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ እገዳ ጥሎበታል።

ተቋሙ መተግበሪያው ላይ የሚጣሉ እገዳዎች ምንም ተፅዕኖ እንዳያመጡ ተደርጎ መሰራቱን ገልፆ ተጠቃሚዎቹ ምንም ስጋት እንዳይገባቸው ተናግሮ ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...