ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ለውጦች የታሰበላቸው አላማ አላሳኩም

Date:



ይህ የተባለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አተገባበር ዙሪያ በተደረገ ውይይት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ትምህርት ኮሌጅ ባልደረባ የሆኑት በላይ ተፈራ(ፕ/ር) በዚህ ዙሪያ የመወያያ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

75 ዓመታት ባስቆጠረው የኢትዮጵ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ታሪክ ውስጥ በርካታ ለውጦች ቢደረጉም ያሰቡት ግብ ማሳካት አልቻሉም ብለዋል፡፡

ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋነኞች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል ለውጦች ሲደረጉ ከታች እስከላይ ያለው አመራር በትክክል ተረድቶ አይሰራውም፣ ወዲያው የመጣው ለውጥ ውይይት ሳይደረግበት በጥናት ሳይደገፍ ይተገበራል ይላሉ፡፡

ከ75 ዓመት በፊት ሲጠየቅ የነበረው ጥያቄ የኢትዮጵ ከፍተኛ ትምህርት ሀገርኛ አይደሉም የሚል ነበር አሁንም ድረስ ይህ ጥያቄ አለ ሲሉም ያብራራሉ፡፡

በላይ ተፈራ(ፕ/ር) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለውጥ ሲያደርጉ አካባቢውን በተገቢው መንገድ ማየት አለባቸው ሲሉም ነግረውናል፡፡

አሁን የመጡ ቴክኖሎጂዎች ፈጣን ለውጦች እንዲመጣ እያደረጉ ነው፤ ምሁራን ለዚህ ዝግጁ መሆን አለባቸውም ይላሉ ፕሮፌሰር በላይ ተፈራ፡፡

የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንደ ከዚህ ቀደሙ ተማሪዎችን በተለመደ የማስተማር ስነዘዴ ማስተማር የለባቸውም ቴክኖሎጂዎች ይህንን ቀይሮታል ከዚህ ቀደም ከነበረው የማስተማር ስነዘዴ የተሻለ አስተምህሮትን መከተል አለባቸው ሲሉም ይመክራሉ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረጉ ለውጦች በአንድ ጀንበር ለመፈፀም መሞከር የለበትም፣ ውይይቶች ጥናቶች ሊደረጉበትና ለውጡ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን በምርምር መረጋገጥ አለበት ይላሉ ፕሮፌሰሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ቴክኖሎጂን መግፋት አይችሉም ይልቁኑ ይህንን ለመተግበር የሚያስችላቸው ስትራቴጂ እንደ ተቋም መንደፍ እና መተግበር አለባቸው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...