የእስራኤል ጦር ጥቃቱን ማጠናቀቁን ሲገልጽ፣ ተመድ በአስቸኳይ ሊሰበሰብ ነው

Date:

በኢራን ላይ የተፈጸመው ጥቃት

የእስራኤል መከላከያ ኃይል “በኢራን አገዛዝ” ላይ አካሄድኩ ያለውን “መጠነ ሰፊ ጥቃት” ማጠናቀቁን ሲያስታውቅ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ነው።

እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት ቅዳሜ ጠዋት በኢራን ላይ በከፈተችው ጥቃት “አንዱ ዒላማ የነበረው በምዕራባዊ ኢራን ኬርማንሻህ አካባቢ ያለው ዘመናዊ የአየር ጥቃት መከላከያ ሥርዓት” እንደነበረ የእስአኤል ጦር ገልጿል።

ጦሩ በመግለጫው የተፈጸሙት ጥቃቶች “የኢራን አብዮታዊ ዘብ አቅምን ለማዳካም እና በእስራኤል ላይ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን ለማምከን የእስራኤል አየር ኃይል በኢራን አየር ክልል ውስጥ የሚያካሂደውን ጥቃት ያለ እንቅፋት ለመፈጸም የሚሰስችል ነው” ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ቅዳሜ በኒው ዮርክ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ በተፈጸመው ወታደራዊ ጥቃት ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።

ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ባህሬን፣ ኮሎምቢያ፣ ቻይና፣ ሩሲያ እና ፈረንሳይ ሲሆኑ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ቀደም ብለው “በመካከለኛው ምሥራቅ የታየውን ወታደራዊ ጥቃት” አውግዘዋል።

ዋና ፀሐፊው ባወጡት መግለጫ ወታደራዊ ጥቃቶቹ ዓለም አቀፍ ሰላምን እና ደኅንነትን የሚጎዱ በመሆናቸው “በአስቸኳይ እንዲቆሙ” ጠይቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...