የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ለአስር ቀናት ይቆያል

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚቀመጡበትን ቅደም ተከተል በተመለከተ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት በይፋ አስጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ሀይሉ፥ ቦርዱ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሀዊ፣ ገለልተኛ እና ስኬታማ እንዲሆን በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህ አካል የሆነ እና በምርጫው የሚወዳደሩ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚቀመጡበት ቅደም ተከተልን  የሚወስን የእጣ ማውጣት ስነስርዓት በዛሬው እለት በይፋ መጀመሩንም ተናግረዋል።

የእጣ ማውጣት ሂደቱ ግልጽ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒ እንዲሆንም የአሰራር ስርዓቶች መዘርጋታቸውም ተገልጿል።

የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆይ መሆኑንም ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

የእጣ ማውጣት ሂደቱን የሚመራ፣ የእጣ አወጣጥ መርሀግብሩን የሚከታተል፥ ፓርቲዎች ወይም እጩዎች መገኘታቸውን የሚፈትሽና ቅሬታዎች ሲኖሩ የሚቀበል አካል መዘጋጀቱም በመርሀግብሩ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...