የከባድ ሚዛን ቦክሰኛዉ ጆርጅ ፎርማን በሞት ተለየ

Date:

“ቢግ ጆርጅ” በመባል የሚታወቀው አሜሪካዊው ጆርጅ በስፖርቱ እጅግ አስደናቂ ስራዎችን በመስራት በ19 አመቱ በ1968 የኦሎምፒክ ወርቅን በማሸነፍ እና የአለምን የከባድ ሚዛን ዋንጫ በ21 አመት ልዩነት ሁለት ጊዜ በማግኘት ዝናን ያተረፈ ነበር።

ጆርጅ ፎርማን ለ 10 ዓመታት ጡረታ ከወጣ በኋላ እ.ኤ.አ. በ1987 በ38 ዓመቱ ወደ ቦክስ ተመልሶ በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ ለዘርፉ የማይተካ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ባለፉት 80 አመታት ከ25 ምርጥ ቦክሰኞች አንዱ መሆን የቻለም እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ጆርጅ ፎርማን በ76 አመቱ ህይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ በማህበራዊ ሚድያ ማስታወቃቸዉን በርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...