የካቮድ ኮሜርሻል “እፎይታ ኤክስፖ” ለሕዝብ ክፍት ነው

Date:

ካቮድ ኮሜርሻል ሪል ስቴት “ዘመናዊ የንግድ ቦታ፤ ከኪራይ እፎይታ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ልዩ የሽያጭ ኤክስፖ በጊዮን ሆቴል በሕዝብ እየተጎበኘ ነው።

ከግንቦት 8 ጀምሮ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆየው ልዩ ኤክስፖ እስከ 40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ይዞ ቀርቧል።

በሁሉም የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነጋዴዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎችና ድርጅቶች ምቹ የክፍያና የባለቤትነት አማራጮች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ደንበኞች ያለምንም ተጓዳኝ ወጪ በቀጥታ ከአልሚው ድርጅት ጋር በመወያየት የሱቅና የቢሮ ባለቤት መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።

የካቮድ ኮሜርሻል በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ግዙፍ የንግድ ማዕከላትን በአዲስ አበባ ለመገንባት ያቀደ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የ3ቱ ግንባታ ተጀምሮ እየተፋጠነ ይገኛል።

4ኛው ሞል ደግሞ በሰኔ ወር በመሃል መርካቶ ግንባታው በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል። ተቋሙ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እና ዘመናዊ አሰራሮችን በመጠቀም የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ እየሰራ ከመሆኑም በላይ፣ ወደ ህዝብ ኩባንያነት ለመለወጥ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እንደማያገኙ ተነገረ

በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በበቂ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችል...

ገዳ ባንክ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ

ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ113 በመቶ እድገት አሳይቷል ...

እስራኤል የኢራን ተደራዳሪዎችን ለመግደል እያሴረች እንደነበር ተዘገበ

አሜሪካና ኢራን ወሳኝ የሆነውን የተኩስ አቁም ስምምነት በደረሱበት እስራኤል...

ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው በፋብሪካ የተቀነባበረ  የበሬ ሥጋ ንግድ ተጀመረ

‘ራንቸርስ ፋይነስት’ የተባለው የኡጋንዳ የግል ሥጋ አቀናባሪ ኩባንያ፣ በየወሩ...