የውሃ አካል ዳርቻ አወሳሰን ልማት እና እንክብካቤ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

Date:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው የውሃ አካል ዳርቻ አወሳሰን፣ ልማት እና እንክብካቤ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ደምጽ አጽድቋል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

የውሃ አካል ዳርቻን በዘላቂነት ለማልማትና መንከባከብ የውሃ ሥነ-ምህዳር አግልግሎትን በማሻሻል ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የውሃ አካል ወንዝ ዳርቻን፣ ሐይቅ፣ ግድብ፣ ውሃ አዘል መሬት፣ ምንጭ እና የከርሰ ምድር ውሃ አያያዝ እና አጠቃቀምን የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መሆኑንም የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አመላክተዋል፡፡

በተከለለ የውሃ አካል ዳርቻ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ነባር ልማት ባለበት ሁኔታ ሊቀጥል የሚችለው በውሃ አካሉና ብዝሃ ሕይወቱ ላይ ጉዳት እና ብክለት የማያስከትል መሆኑ አግባብ ባለው አካል ሲረጋገጥ ስለመሆኑም አስገንዝበዋል፡፡

“የውሃ አካል ዳርቻ ልማትና እንክብካቤ የአካባቢ ማህበረሰብን በሚያሳትፍ እና ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ አግባብ ባለው አካል ታቅዶ እንዲተገበር ይደረጋል” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ ልማትን ለማፋጠን እና የወንዝ ዳር አትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን የምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

የውሃ አካል ዳርቻን ማልማት በአዋጅ መደንገጉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ወንዞች በደለል እንዳይሸፈኑ ለመከላከል እንደሚያግዝም የገለጹም ሲሆን የአፈፃፀም መመሪያ በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀው ፍሳሽ ለወንዝ ዳርቻው የብክለት መንስኤ እየሆነ የመጣ በመሆኑ ይህን ለመከላከል እና ለመቆጣጣር በአዋጁ መመላከት እንዳለበት የምክር ቤት አባላት ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምክር ቤቱ የውሃ አካል ዳርቻ አወሳሰን ልማት እና እንክብካቤ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1382/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...