የጂቡቲው ፕሬዚዳንት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቀጣናውን እያተራመሰች ነው ሲሉ ከሰሱ

Date:

ፕሬዚዳንቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ወታደራዊ መስፋፋትን በውስጡ የያዘ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌህ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ የምታደርገው የ110 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት በኢኮኖሚ ልማት ሽፋን ወታደራዊ መስፋፋትን በውስጡ የያዘ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሃገሪቷን አካባቢው እንዳይረጋጋ እያደረገች ነው ብለው ሲከሱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወደብ እና ቴሌኮሙኒኬሽን በመሳሰሉ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚታዩ አጋርነቶች ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ሳይሆን ያላቸው የአፍሪካ ሃገራትን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ወታደራዊ አላማዎችን የያዙ ናቸው ብለዋል።

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት በተጨማሪ ከዚህ በፊት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በእኛ  ወደብ ላይ ወታደራዊ ሰፈር ለመገንባት ጠይቃ ጥያቄዋን ስላልተቀበልን ትኩረቷን ወደ ጎረቤት ሃገሮች አድርጋለች ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአካባቢው ኢኮኖሚን ከወታደራዊ ትብብር ጋር የቀየጡ አካሄዶች ስጋተ ናቸው ያሉ ሲሆን ሁኔታዎቹ የኛን ሉዓላዊነት እንዳይሸራርፉ በአትኩሮት እንከታተላለን ብለዋል።

ጂቡቲ በአሁኑ ወቅት እንደ አሜሪካ፣ቻይና፣ፈረንሳይ እና ጃፓን ላሉ ሃገራት ወታደራዊ ሰፈሮችን በባህሯ ላይ መስጠቷም ይታወቃል።

Source: All East Africa

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...