የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ የታክስ ኦዲት መመሪያ አወጣ

Date:

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት አፈጻጸምን እና የታክስ ስሌት ማስታወቂያ አወጣጥን የሚመራ አዲስ መመሪያ ቁጥር 1063/2017 አውጥቷል። መመሪያው በትላንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የወጣ ሲሆን፣ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ግልጽ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ አዲስ መመሪያ የታክስ ባለሥልጣን ባለሙያዎችንና ታክስ ከፋዮችን ኃላፊነት የሚደነግግ ሲሆን፣ በተለያዩ የታክስ ኦዲት ዓይነቶች ላይ፣ እንደ የተመላሽ ኦዲት፣ የዴስክ ኦዲት፣ ጭብጥ ተኮር ኦዲት፣ አጠቃላይ ኦዲት እና የማጭበርበር ምርመራን ጨምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል።

መመሪያው የፌዴራል መንግስትን የታክስ አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ የተሟላ ማዕቀፍ እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም የኦዲት ሂደቱ ወጥነት ያለው፣ ግልጽነት የሰፈነበት እና የታክስ ከፋዮች መብት የሚጠበቅበት መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ተመላክቷል።

የታክስ ስሌት ማስታወቂያ የሚላከው ታክስ ባልተከፈለበት፣ ተጨማሪ ታክስ እንዳለ ሲረጋገጥ፣ ወይም ታክስ ማጭበርበር ጥርጣሬ ሲኖር የተባለ ሲሆን የመስክ ኦዲት ከመጀመሩ አስር የስራ ቀናት በፊት ለታክስ ከፋዩ የጽሁፍ ማስታወቂያ መሰጠት እንዳለበት ካፒታል ከመመሪያው ለመረዳት ችሏል።

ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ታክስ ከፋዮች ለኦዲተሮች ምቹ ሁኔታዎችን የማመቻቸትና የሚጠየቁ ሰነዶችን የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ያሳስባል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...