”የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ነኝ”- ተመድ

Date:

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ የገንዘብ ቀውስ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል አስጠነቀቀ።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፥ የህብረቱ አባል ሀገራት እዳቸውንና ክፍያቸውን በአግባቡ ባለመክፈላቸው ምክንያት ድርጅቱ “የገንዘብ ውድቀት” ስጋት ላይ መውደቁን ገልጸዋል።

የገንዘብ አቅርቦትቱ እስከ ሐምሌ ወር ድረስ ብቻ ሊያዘልቅ የሚችል ነውም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ከገንዘብ ቀውሱ ለመትረፍ ለ193ቱ አባል ሃገራት ውዝፍ እዳቸውን እንዲከፍሉና የድርጅቱን የፋይናንስ ህግ እንዲያሻሽሉ ለአባል ሀገራቱ  ደብዳቤ መጠየቁን ድርጅቱ ገልጿል።

ምንም እንኳን የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በ2025 መገባደጃ ላይ በፋይናንሺያል ስርአቱ ላይ ከፊል ማሻሻያ ቢያደርግም ፣ ከከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ስጋት መትረፍ አልቻለም።

በጄኔቫ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ ስለሁኔታው የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች በየቦታው ተቀምጠዋል።

ጉቴሬዝ በደብዳቤው ላይ የመንግስታቱ ድርጅት ቀደም ባሉት ጊዜያት የገንዘብ ቀውሶች አጋጥመውት እንደነበር ነገርግን አሁን ያለው ሁኔታ “ከሁሉም የተለየ ነው” ሲሉ የነገሩን አሳሳቢነት አንጸባርቀዋል።

ከፀደቀው መደበኛ በጀት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዙ የተገመገሙ መዋጮዎችን ላለማክበር የተላለፉ ውሳኔዎች አሁን በይፋ ተገልጸዋል ያሉት ዋና ጸሃፊው የተወሰኑ አባላትን ሳይጠቅሱ ቀርተዋል።

የአጠቃላይ ስርዓቱ ታማኝነት” በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር መሰረት የሚጠበቀውን ግዴታ በመወጣት ላይ የተመሰረተ ነውም ብለዋል ጉቴሬዝ ።

ከተገመተውን መዋጮ ከጠቅላላው ዕዳ ውስጥ 77 በመቶው የተከፈለው በ 2025 ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁንና በ2026 እያጋጠመን ያለውን የገንዘብ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑ ሲገለጽ፥ ባልተሰበሰበ ገንዘብ በጀት ማስፈጸም እንደማይቻልም እና ድርጅቱ ያልሰበሰበውን ገንዘብ ለመክፈል መገደዱ ተነግሯል።

በደብዳቤው እንደሰፈረው፥ በዚህ ወር ድርጅቱ 227 ሚሊዮን ዶላር  ያልሰበሰብነውን ገንዘብ እንዲመልስ ተገዷል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...