የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት ተቋርጧል

Date:

የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት መቋረጡን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡

የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት የተቋረጠበት ምክንያት፡-

  1. በየአካባቢው የሚገኙ የኢንተርኔትና ሕትመት ቤቶች ጥራት በሌላቸው ካርዶች እያተሙ በመሆኑ፣
  2. የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በፎቶሾፕ እያስመሰሉ በመስራት የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችን እያጭበረበሩ ያሉ አታሚዎች በስፋት መታየታቸው፣
  3. ከከተማ ራቅ ብለው የሚኖሩና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ዜጎች ትክክለኛ ባልሆነ የካርድ ሕትመት እየታለሉ ፤ ገንዘብና ጊዜያቸውን ከመጭበርበራቸው ባሻገር የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ እያደረገ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡

ስለሆነም ዜጎች የኢ-ፋይዳ አማራጭ ሲፈልጉ የ”Fayda ID” ሞባይል መተግበሪያ ላይ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጠቁሟል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...