የፍልስጤማውያን ወደ ጋዛ መመለስ

Date:

በጋዛ የተኩስ አቁም ተግባራዊ መሆን በመጀመሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ መመለስ ጀመሩ፡፡

በእስራኤልና ሀማስ መካከል ያለውን ግጭት እንዲቋጭ በአሜሪካ የቀረበው የሰላም ስምምነት የመጀመሪያው ምዕራፍ መተግበር በመጀመሩ ነው ፍልስጤየማውያን ወደ ሰሜን ጋዛ መመለስ የጀመሩት፡፡

የእስራኤል መንግሥት ተኩስ ማቆም እና ታጋቾችን ብሎም እስረኞችን ለመፍታት የሚያስችለውን የጋዛ ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በትናንትናው እለት ማፅቀዱ ይታወሳል፡፡

በዚህም የእስራኤል ጦር ወደ ተስማሙበት መስመር ወደ ኃላ አፈግፍገዋል። የተኩስ አቁሙ ስምምነት መጀመር ከፍተኛ መጠን ያለው የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ በር ይከፍታል ነው የተባለው።

በዕቅዱ ውሎች መሠረት ሐማስ በሕይወት የሚገኙትን 20 የእስራኤል ታጋቾች በ72 ሰዓታት ውስጥ ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የእስራኤል መንግስት በበኩሉም በእስር ላይ የሚገኙ 250 ፍልስጤማውያንን እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት በጋዛ ታስረው የሚገኙ ተጨማሪ 1,700 እስረኞችን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘገባው የቢቢሲ ነው NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...