ይሄ ጠለፋ ሳይሆን የአንድ ሰው የፍቅር ታሪክ ነው

Date:


ታሪክ የቀየረችው የኤዜ የስልክ ጥሪ


አርሰናል ድምጹን አጥፍቶ ከፈጸማቸው ትልልቅ ዝውውሮች ምን አልባትም ይሄኛው ቀዳሚ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ኤቤሬቺ ኤዜ ከክሪስታል ፓላስ ወደ አርሰናል ያመራበት፡፡

እንግሊዛዊው ሁለ ገብ ተጫዋች በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ስሙ ከአርሰናል ጋር ሲያያዝ ቢቆይም በመድፈኞቹ በኩል ያለው ፍላጎት እየቀዘቀዘ መምጣቱን ተከትሎ ቶተንሀም ዝውውሩን ገፍቶበታል፡፡

እዚህ  ላይ ግን አንድ ነገር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ከሰኔ ወር ጀምሮ ከኤዜ ጋር በቅርበት በዝውውሩ ጉዳይ ሲያወራ ቆይቷል፡፡ የለንደን ተወላጁ ኤቤሪቺ ኤዜ እግር ኳስን የጀመረው በአርሰናል ቤት ነው፡፡ ለዚህ ክለብ የተለየ ፍቅር እንዳለው በተደጋጋሚ ሲናገር ይሰማል፡፡ ይሄንኑም ለክለቡ ያለውን  ክብር ለሚካኤል አርቴታ ሲያስረዳም ቆይቷል፡፡

ኤቤሬቺ ኤዜ እግር ኳስን በአርሰናል አካዳሚ ቢጀምርም የ13 አመት ልጅ እያለ የአካዳሚው መልማዮች በወቅቱ ከእሱ የተሻሉ ታዳጊዎችን በማግኝታቸው እንዲቀነስ ሆነ፡፡ የለንደን ተወላጁ የያኔው ታዳጊ አርሰናልን እየወደደውም ቢሆን ለመለየት ተገደደ፡፡ በዚሁ ምክንያት ለተወሱኑ ቀናቶች ድብርት ውስጥ ገብቶ እንደነበርም ተዘግቧል፡፡

ከዚህ በኋላ ራሱን ለማግኝት ፉልሀም፣ ሪዲንግ፣ ሚልዋል፣ ኩይንስ ፓርክ ሬንጀርስ እና ወይኮምብ ወንድረስ ከቋሚነት እስከ ውሰት ያሳለፈባቸው ክለቦች ሆኑ፡፡ 2020 ላይ ግን ክሪስታል ፓላስ ኤዜን ከኪው ፒ አር በቋሚነት አስፈረመው፡፡ በሌላኛው የለንደን ክለብም ኤቤሬቺ ኤዜ ምርጥ መሆኑን አስመሰከረ፡፡

ሁለገቡ ተጫዋች በፓላስ ባሳየው ድንቅ ብቃት የበርካታ ክለቦች ትኩረት ሆነ፡፡ የእሱ ፍላጎት ግን በአውሮፓ ሻምፒንስ ሊግ የሚሳተፍ ከምንም በላይ ደግሞ ከእግር ኳስ ጋር የተዋወቀበት የልጅነት ክለቡ አርሰናል ነው፡፡ የአርሰናል ዝውውር ካልተሳካ የአርሰናል የምንጊዜም ተቀናቃኝ ወደ ሆነው ቶተንሀም ማምራት 2ኛ እቅዱም ሆነ፡፡

የቶተንሀሙ አማካይ ጄምስ ማዲሰን የጉልበት ጅማት መበጠስ ጉዳት ማስተናገዱ  አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ኤዜን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ወስደዋል፡፡

አርሰናል ኤዜ ላይ ያለው ፍላጎት በተጠበቀው ልክ አለመሄዱን ተከትሎ በክሪስታል ፓላስ እና በቶተንሀም መካከል ያለው ድርድር ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ፡፡ የተጫዋቹም ወደ ነጭ ለባሾቹ ቤት የማምራት ዕድሉ በዚያው ልክ የተቃረበ ሆኗል፡፡

ከክለቦቹ ስምምነት በኋላ የ27 አመቱ ኤቤሬቺ ኤዜ ባለፈው ረቡ ፊርማውን ለቶተንሀም ለማስቀመጥ ቀጠሮ የያዘበት ዕለት ሆነ፡፡

ከዚህ በኋላ አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡

ኤቤሬቺ ኤዜ ፊርማውን ለቶተንሀም ከማስቀመጡ በፊት የመጨረሻ እድሉን ለመሞከር ለአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ አንድ ስልክ ደወለ፡፡

“ለቶተንሀም ልፈርም ነው ወደ አርሰናል የምመጣበት ዕድል አብቅቷል ወይ የሚል መልዕክት ነበር”፡፡ ይቺ የመጨረሻ ስልክ ብዙ ነገሮችን የቀየረች እና ኤዜን ከልጅነት ክለቡ ጋር በድጋሜ እንዲገናኝ ትልቁን በር የከፈተች ሆነች፡፡

ሚካኤል አርቴታም የካይ ሀቨርዝን ጉዳት በተመለከተ ከቦርዱ ጋር ስብሰባ አድርጎ ስለበር በጀርመናዊው አጥቂ ቦታ ሌላ ሰው በማስፈለጉ ኤቤሬቺ ኤዜ  በአርሰናል የሚፈለገው ሰው ሆነ፡፡

በሦስት ቦታ የሚጫወተው ኤዜም ለቶተንሀም የመፈረም ሃሳቡን  በብርሀን ፍጥነት ቀይሮ ወደ አርሰናል ለማምራት ይሁንታውን ገለጸ፡፡ ረቡዕ ዕለት ለቶተንሀም ይፈርማል የተባለው ኤዜ የዚያኑ ቀን ሁሉንም ነገር ከአርሰናል ጋር ጨረሰ፡፡

ይሄ ዜና ከተሰማ በኋላ ወትሮም ከጎረቤታቸው አርሰናል ጋር በትልቅ ተቀናቃኝነት የሚተያዩት የቶተንሀም ደጋፊዎች እና የስራ ሃላፊዎች አስደንጋጩን ነገር ከመቀበል ውጭ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡

የ27 አመቱ ኤዜም በድጋሜ ወደ አርሰናል ለመመለስ የመድፈኞቹ ተጫዋቾችን ጭምር ለማሳመን ያደረገው ጥረት ተሳክቶለት  ከ14 አመታት በኋላ ወደ ኢምሬትስ ተመለሰ፡፡

የቶተንሀም ሰዎችን ጨምሮ ብዙዎች አርሰናል ተጫዋቹን ከቶተንሀም ሆትስፐር እንደ ጠለፈው ሊያስቡ ይችላሉ ነገር ግን ይሄ ኤቤሬቺ ኤዜ ለአርሰናል መለያ ያለውን ፍቅር እስከ መጨረሻው ሰአት ያሳየበት እና ያሳካበት የፍቅር ታሪክም ሆነ፡፡

ምሽት አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 5 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ከደጋፊዎቹ ጋር ሲተዋወቅ ፊቱ ላይ የሚታየውም ደስታ የዚሁ ማሳያ ነበር፡፡

#eberechieze

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...