ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን የሚያስችል “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ አዲስ ዲጂታል የክፍያ አገልግሎት በሸራተን አዲስ ሆቴል በዛሬው ዕለት አስተዋዉቋል።
በዳሸን ሱፐር አፕ መተግበሪያ ውስጥ የተካተተው ይህ አገልግሎት ደንበኞች ያለ ሂሳብ ቁጥር፣ ያለ ኪውአር (QR) ኮድ ወይም ያለ ስልክ ቁጥር በአቅራቢያቸው የሚገኙ የንግድ ተቋማትን በቀላሉ በመምረጥ እና ምስጢራዊ የፒን (PIN) ቁጥራቸውን በማስገባት በሰከንዶች ውስጥ ክፍያ እንዲፈፅሙ ያስችላቸዋል ተብሏል።
የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በምረቃው ላይ እንደገለጹት፣ ባንኩ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል። አክለውም “በኤር ፔይ የክፍያ መፈጸሚያ መንገድ ብቻ ሳይሆን ደንበኞቻችንን ከሀገር ውስጥ የንግድ ተቋማት ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ አማራጭ ፈጥረናል” ብለዋል።
በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት የሚያጠናክረውና በነጋዴዎችና በደንበኞች መካከል ያለውን የግብይት ክፍተት ያጠባል የተባለው “ዳሸን ኤር ፔይ” ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።
የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን አስታወቀ
የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል።
