የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአክሲዮስ (Axios) ሚዲያ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ-መጠይቅ፤ በኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ የሀገሪቱ ህዝብ ሲያለቅስ ማየታቸው በእጅጉ እንዳስገረማቸው አልጀዚራ ዘግቧል።
ትራምፕ በሰጡት አስተያየት «ህዝቡ በሙሉ የሚጠላው ይመስለኝ ነበር» በማለት ተገርመው ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም የኢራን ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ በቀብሩ ላይ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው ስለሚገኙ አሜሪካ «ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማጥፋት» የምትችልበት የጦርነት አቅም እንዳላት ጠቁመው፤ ነገር ግን ይህንን ዛቻ ተግባራዊ ካደረጉት «ለመደራደር የሚተርፍ ሰው ስለማይኖር» ጥቃቱን ከመሰንዘር መቆጠባቸውን በግልጽ ተናግረዋል።
ትራምፕ ለሚዲያው እንደገለጹት፤ አሜሪካና ኢራን የኻሚኒ የቀብር ስነ-ስርዓት እስኪጠናቀቅ ድረስ በድርድርም ሆነ በወታደራዊ ግጭቶች ላይ ጊዜያዊ እረፍት ለመውሰድ ተስማምተዋል። በመሆኑም «በቀብር ስነ-ስርዓቱ ሂደት ወቅት የትኛውም ወገን በሌላው ላይ ጥይት አይተኩስም» ሲሉ አረጋግጠዋል።
